ሰውነት

ሥጋህ ይመዘናል ለገበያ ይቀርባል ደምህ ይወቀሳል ዘርህ ይቆጠራል የቆዳህ ቀለም ወይ በር ያስከፍታል ወይ ያዘጋብሃል ኑሮን ስትታገል ሲኖርህ ሰው ታፈራለህ ስታጣ አስታዋሽ የለህ ሲሳካ ፈላጊህ ብዛቱ ስትከሽፍ ብቸኝነቱ መኖርን ትኖራለህ ተስፋ ሆኖ ምግብህ   የሰውነትህ ዳገት ቁልቁለቱ እስከ ሞት እኔነትህ ተፈትጎ ተበጥሮ ተወቅጦ ተለስኖ ተመርጎ ተወቅሮ ተለንቅጦ ስቀህ አልቅሰህ ጠግበህ ተርበህ አፍቅረህ ጠልተህ ናፍቀህ ረስተህ ጉዞ ወደፊት…   *** Continue reading ሰውነት

Poem of the Day

The following Afaan Oromo poem is written by Moti Abelti Tufa. One of our readers forwarded it to us. Moti wrote the poem to express his happiness that Afaan Oromo will join the BBC World Service programming as one of the languages from the Horn of Africa, along with Amharic and Tigrigna. The poem celebrates those who participated in the #BBCAfaanOromo online petition, asking the … Continue reading Poem of the Day

ፀሐይ ትወጣለች ይህም ያልፍና!

ልብ የሚያደማ ሐዘን የወንድም አንገት ሲቀላ በአረመኔ ሰው ቢላ! እጅግ የሚያስመርር ሰቀቀን እህት እንደወጣች ስትቀር ሳያልፍላት በባዕድ ምድር! ህዝብ ሲቆጣ፣ ሲያለቅስ ስሜቱ ፈንቅሎ እየወጣ እንባ አባሽ መሪ ግን አጣ! ለነገሩ የሚገርፍ፣ የሚከርችም የህዝብን ድምፅ የሚያፍን እንዴት ብሎ እንባ አባሽ ይሁን?! በብዕር የታገለውን፣ በሽብር ስም ወህኒ ቤት ውስጥ ያጎረ መንግስት ለዙማና ኣይሲስ ከየት ሊያመጣ ስሜት?! ልብ የሚያቆስል ግፍ በሀገር ውስጥ፣ ከሀገር ውጭ የወጣት ተስፋ ሲቀጭ፤ በንዴት … Continue reading ፀሐይ ትወጣለች ይህም ያልፍና!

ፌስቡከኛ ፍቅር

ፍቅርም ዘምኖ ቋንቋው ፌስቡከኛ ከዓለም መንኖ የሳይበር ደንበኛ በፎቶ መማረክ add፣ add መደራረግ በlike ወይም በpoke ዒላማን መፈለግ ሲጀመር መግባባት “ቶሎ ነይ”፣ “ቶሎ ና” ያለምንም ትዕግስት ልብ ይሰክርና በinbox መሳሳብ በቃላት ትውውቅ መመሰጥ በሐሳብ ጭራሽ መነፋፈቅ በemoticon መግለጽ ውስጣዊ ስሜትን በዓለም ላይ ማመጽ አምልኮ ሳይበርን ልዑሉ፣ ልዕልቷ  ፌዝቡክ ላይ ይነግሡና ውበቱ፣ ውበቷ መለኪያ ያጣና   የperfect ማንነት ይፈበረክና ድንቅ የሆነ ሰው ባምሮ ይሳልና ፆታ ወንድ … Continue reading ፌስቡከኛ ፍቅር

ለካስ…

በሕልሜ ወንዝ አየሁ ረዥም ጥቁር ወንዝ እንደ ዘንዶ የሚጠማዘዝ ዘልዬ እንዳልዋኝ ፈራሁ “ቢውጠኝስ” ብዬ… ወንዙ በዝምታ ሲፈስ    ውስጤ በሐሳብ ሲታመስ ለካስ ልደት ነው ዛሬ በትዝታ ጭልጥ ወዳገሬ ቦቃ ፈረስ እየጋለብኩ ውቅያኖሱን ልሻገር ስል… ብንን እዚህ አዲስ ዘመን ቀዝቃዛ ወላፈን *** መልካም ገና! Continue reading ለካስ…

ማርያምን!

አንቺ ነሽ የኔ ፋሲካ ፍቅርሽ ልብ የሚያረካ አምሮብሻል የሀገር ባሕል ለብሰሽ ዘንጠሻል ውዴ የኔ ጣፋጭ ስትይ ቀጭ ቋ ቀጭ አረማመድሽ ሲያምርብሽ አንቺ የኔ ቆንጆ ልዝፈንልሽ ዋጆ የኔዋ ፈንዲሻ የኔ ልበልሻ አንቺ የኔ አማላይ የኔዋ ውብ ፀሐይ ደማቅ የማለዳ ቀይ ጽጌረዳ ማርያምን! *** Continue reading ማርያምን!

ከልብ ሲዋደዱ

ከልብ ሲዋደዱ ደስ ይላል መንገዱ ተውቦ ባበቦች ደምቆ በኮከቦች ታጅቦ በቀልዶች በሳቅ በጫወታ በሚስብ ፈገግታ በሚጥሙ ቃላት በሚያምሩ ቀለማት ከልብ ሲዋደዱ በፍቅር ሲያብዱ ምስጢር አይቋጥሩ ተማምነው ይኖሩ ጥል እንኳ ቢፈጠር ውሎ የማያድር ሆድ ውስጥ የማይጠጥር ረምጦ የማያሳር በይቅር ይቅርታ ሳይከር የሚፈታ የግልጽነት ጉዞ ነገር ሳይሆን አዞ የሚባላ አራዊት ሳይታሰብ ድንገት ከልብ ሲዋደዱ ምቹ ነው መንገዱ ጎርባጣ እንኳ ቢሆን አያስመር አያስመንን *** “[When] you find someone … Continue reading ከልብ ሲዋደዱ

በልዩነት አንድነት (Unity in Diversity)

አንድነት የአብሮ መኖር መሠረት በግዴታ ሳይሆን በውዴታ በሚገነባ ቤት ልዩነትን የማይሽር የማይሰርዝ የማይፍቅ የአንዱን የበላይነት የማያደምቅ ሌላውን በኃይል የማይደፍቅ የተለየን የማይገፋ የማያጠወልግ ራስን መሆን ራስን ማስተዳደር የማይነፍግ በወንድማማችነት በእህትማማችነት መንፈስ የተሳሰረ ቤተሰባዊነት የሚያስቀድም ሰብዓዊነት የማያስር የማይገድል ያልሆነ ፍርደ ገምድል የማያባር የማያፍን የማይነዳ ወደ ገደል የማይጨቁን የማያደማ የማይደፈጥጥ የሚያለማ ከነጻነት ጋር ከቢሊሱማ ከሓርነት ጋር በሰላም ዜማ! *** *** We all are pencils, but we come in different colors, … Continue reading በልዩነት አንድነት (Unity in Diversity)