ተከላካዩ

ጎል አዳንኩኝ ብሎ አጥቂን አንከባሎ ቅጣት በማግኘቱ ሐዘን እንባ ፊቱ በገዛ ጥፋቱ የዋልያው ጀግና ሽንፈትን በመፍራት አጥቂን ጎተተና ተከላከል ቢሉት ተደናበረና የኳስ ደንብ ጥሶ ጥሎ ማለፍ ቢያምረው አረፈ ጎል ቀምሶ ከሸፈና ሴራው በወሳኝ ጨዋታ ንስሩን በደስታ ሸኘ እሱ አልቅሶ ከአንድ እኩል አንሶ የቡድኑ ጥረት ግሩም አጨዋወት አላመጣ ውጤት በአንድ ሰው ጥፋት *** In the Amharic piece above, I reflect on the Ethiopia vs Nigeria football … Continue reading ተከላካዩ

ሣንሱረኛ (The Censor)

ሣንሱረኛ … ሣንሱረኛ አሳረኛ ክፉ መቀስ ለግል ፕረስ… መከራከር መደራደር እንዳይሰምር ማነቅ መንከስ ምላስ መቁረጥ ወይ ማንቀጥቀጥ በፍርሃት ውርጭ ማርገፍ አገጭ ሣንሱረኛ ነገረኛ አፋኝ አምካኝ ፈላጭ ቆራጭ ዶማ ምላጭ የመጻፍ ፀር የመናገር መብት እንዳይኖር ሣንሱረኛ የማይተኛ ትችት ሮሮ የማይሰማ በገጠሩ በከተማ አዲስ ሐሳብ የሚፈራ የማይጓጓ ለፈጠራ የሚለፋ ለኪሳራ ሣንሱረኛ መከረኛ… …እውነተኛ ጋዜጠኛስ የትኛው ነው— ፖለቲካ ያልበከለው አሉባልታ የማይጽፈው? *** Freedom of the Press and Censorship … Continue reading ሣንሱረኛ (The Censor)

የአርበኞች መንፈስ ሲታወስ (Remembering Ethiopian Patriots)

February 19, or Yekatit 12, is remembered in Ethiopia as Martyr’s Day. Seventy six years ago, two young Ethiopians (they were Eritreans but Eritrea was a province of Ethiopia then), Abraham Deboch and Moges Asgedom, who were angered by racism and colonial occupation, attempted to assassinate Rudolfo Graziani, the commander of the Italian fascist forces that occupied Ethiopia between 1936-1941, inflicting heavy wounds on him and … Continue reading የአርበኞች መንፈስ ሲታወስ (Remembering Ethiopian Patriots)

እስከመቼ?

እስከመቼ? እስከመቼ በጉልበት መነጣጠቅ ሥልጣንን በትንቅንቅ? እስከመቼ በሽኩቻ ሀገርን ማድረግ ገወቻ? እስከመቼ መሆን ሙጫ ያለዲሞክራሲ ምርጫ? እስከመቼ ወንጃ ወንጃ መፍትሔ መሻት በጠበንጃ? እስከመቼ…? እስከመቼ…? እስከመቼ ወተምተም ወተምተም አረጋግዞ ጥላቻና ቂም? እስከመቼ እንጎድ እንጎድ በመብረቅ ድምፅ በነጎድጓድ? እስከመቼ ቃሰንተኛ የሙስና ሱሰኛ? እስከመቼ ማቶንቶን ያለነፃነት መታፈን? እስከመቼ መርገጥ ጭቅጫቅ ያለ ፍትህ መንቦራጨቅ? እስከመቼ…? እስከመቼ…? እስከመቼ መጠላለፍ እያመጹ ጥሎ ማለፍ? እስከመቼ ምቀኝነት በቀልና መጥፎ ቅናት? እስከመቼ አምባገነን እየሾሙ … Continue reading እስከመቼ?

መሞጋገስ

እነሱ እሷ እሱ እርስ በርስ ሲሞጋገሱ እነዛን ሲወቃቅሱ ሌባ ጣትን ቀስረው ሦስቱን ጣቶች ረሷቸው በመሞጋገስ ሰክረው እኔ እኛ እሳቸውስ እርስ በርስ ስንሞጋገስ እነዛን ስንወቃቅስ ሌባ ጣትን ቀስረን ሦስቱን ጣቶች ረስተን በሙገሳ አልሰከርን? (ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ሌላን ሲወቅሱ) *** What can everyone do? Praise and blame. This is human virtue, this is human madness. —Friedrich Nietzsche You can’t let praise or criticism get to you. It’s a weakness … Continue reading መሞጋገስ

ነጭ ጠቃሽ

ፍራሽ አዳሽ እንጂ ፍራሽ ሰሪ ጠፍቶ ነጭ አምላኪ ጥቁር ነጭ ጠቃሽ በዝቶ የሌላን አፍቃሪ የራሱን አጥላልቶ የሚሸምት ሰልባጅ የፈረንጅ ድሪቶ አንዴ “ማርክሲዝም” አንዴ “ሌኒንዝም” አንዴ “ሊብራሊዝም” ሲመቸው “ሰርድ ዌይ” ሲከፋው “ዲስትሮይ” ባላገር ገርሞት ዝም ብዙ እየሰማ ዝም ዝምታው ሲገርም ቁዝምዝም ቁዝምዝም እያየ የተማሩ ሲቀበዣዥሩ አንዴ “ሪቮሉሽን” አንዴ “ኢቮሉሽን” አንዴ “ዲሞክራሲ” አንዴ “ቢሮክራሲ” ያሁን ደግሞ “ፋሽን” “ዲኮንስትራክሽን” “ትራንስፎርሜሽን” ቀርቶ “ዳያሌክቲክ” በርክቶ ንትርክ ሳይቀር ሆድን ማከክ ከዘመን … Continue reading ነጭ ጠቃሽ

የከንፈርሽ ፊርማ (Signature of Your Lips)

የከንፈርሽ ፊርማ ከንፈሬ ላይ አርፎ ገላሽ ከገላዬ ሲደንስ ተቃቅፎ ልብሽ ከልቤ ጋር ገነት ገባ ከንፎ ሲቃሽ ጆሮዬ ውስጥ እንደ ዜማ ጦፎ *** Singnature of your lips lands on mine As our bodies dance Our hearts fly to heaven Your ‘aah’ melody in my ears *** Continue reading የከንፈርሽ ፊርማ (Signature of Your Lips)

ምድርና ሰማይ እንዴት ተለያዩ? (Why the Earth & the Sky Separated)

ምድር ውብ ፀሐይን፣ ምድር ውብ ጨረቃን ሲያፈቅር፤ ተለያዩ፣ እሱና ሰማዩ። *** When the earth fell in love With both the charming sun And the charming moon, That was indeed why the sky and him separated. Continue reading ምድርና ሰማይ እንዴት ተለያዩ? (Why the Earth & the Sky Separated)