የከንፈርሽ ፊርማ (Signature of Your Lips)

የከንፈርሽ ፊርማ ከንፈሬ ላይ አርፎ ገላሽ ከገላዬ ሲደንስ ተቃቅፎ ልብሽ ከልቤ ጋር ገነት ገባ ከንፎ ሲቃሽ ጆሮዬ ውስጥ እንደ ዜማ ጦፎ *** Singnature of your lips lands on mine As our bodies dance Our hearts fly to heaven Your ‘aah’ melody in my ears *** Continue reading የከንፈርሽ ፊርማ (Signature of Your Lips)

ካንቺ ጋራ ፍቅር

ጣቶችሽ አለንጋ አቤት ሲያናዝዙ ካንቺ ጋራ ፍቅር ብዙ ነው መዘዙ አቤት ቁንጥጫቸው ግርፊያቸው መከራ ትንፋሽሽም እሣት የስሜት ደመራ ቧጥጠሽ ቧጥጠሽ የጀርባዬን ሥጋ ዱላ ነው ፍቅርሽ ሌሊቱ እስኪነጋ መግነጢሳዊ ኃይል ገላሽ እየሳበኝ ለማምለጥ አልቻልኩም እንደ ወጥመድ ይዞኝ *** Continue reading ካንቺ ጋራ ፍቅር

ሥብራት

በመንፈስ ሥብራት ቁስሌ አመርቅዞ ምሬትን አርግዤ በጨለማው ጉዞ ዓይኖች ሳያዩኝ ወደ ሲዖል መንደር ዕዝኔ ቢያዳምጥም አፌ አይናገር ሐዘንን የሚያርቅ ልቤ ፍቅር አጥቶ ውስጤ ማቅ ለበሰ እንደ ጉም አጥልቶ መንፈሴ አልሰክን እያለ ደንፍቶ ደሜ ገነፈለ እንደ ቡና ፈልቶ ልክ እንደ በረዶ እኔነት ቀዝቅዞ ሰላሜ ተናጋ ተስፋዬ ደብዝዞ ስሜቴም ለዘዘ አዕምሮዬ ፈዞ ሞት ግን ፈነጠዘ መስሎት የምናዘዝ እሱን ሳላወግዘው በቁሜ ምገነዝ *** Continue reading ሥብራት