የሽንት ቤት ቀን

የሽንት ቤት ዝግመታዊ ለውጥ፦ ሰገራ ቤት፥ መቀመጫ ቤት፥ ሽንት ቤት፥ መፀዳጃ ቤት።

በጆክ ወይም ጣሳ ውሃ፥ በኮባ ቅጠል፥ በዘበርጋ ሱቅ ስኳር መጠቅለያ የውጭ ሀገር ጋዜጣ ወይም ወረቀት፥ በሶፍት።

ሜዳ፥ መንገድ ዳር፥ ቁጥቋጦ፥ የተከለለ ጉድጓድ፥ ፖፖ፥ ባኞ።

ኢትዮጵያ ውስጥ በሽንትቤት እጦት የማይንገላታ የሀገር ሰው ቢኖር ጥቂት የተደላደሉት ባለሀብቶች ብቻ ናቸው። ሽንትቤት የኋላ ቀርነታችን ትልቁ ማሳያ ነው። “ሀበሻ ምግቡን ይደብቃል፤ ሰገራውን ግን በግልፅ ሜዳ ላይ ይፀዳዳል” ያለው ማን ነበር?

ድህነት ብዙ ዓይነት መገለጫዎች አሉት። የንፅህና ጉድለት ግምባር-ቀደሙ ነው። የንፅህና መጉደል ደግሞ የጤና ጠንቅ ነው። ኮሶ፥ ወስፋት….ቅማል፥ ቅጫም፥ እከክ… ወዘተ።

አብዛኛው የሀገሪቱ ሕዝብ የረባ መፀዳጃ ቤት የለውም። አንዳንድ ቦታ ለአንድ ብዙ አባወራዎችንና እማወራዎችን ላቀፈ ግቢ አንድ ሽንት ቤት ብቻ ይሰራል። ያ ማለት ጠዋት ሰው ወረፋ ይዞ መጠበቅ አለበት። መጠበቅ ያልቻለው ደግሞ ቁጥቋጦ ወይም ሻይ ቤት ፍለጋ ሩጫ።

ስንታችን ነን ሰፈራችን አሪፍ ሽንት ቤት ያለን? ስንታችንስ የሕዝብ ሽንት ቤት እንጠቀማለን? የክፍለሀገሩ ችግር እንዳለ ሆኖ አዲስ አበባስ የትኛው የረባ የሕዝብ ሽንት ቤት አላት? ስንታችሁ ናችሁ ሽንታችሁን ቋጥራችሁ፥ ሽንት ቤት ፍለጋ ለሰዓታት የሮጣችሁ፥ ለመጠቀም ደጅ የፀናችሁ?

የትምህርት ቤትና የካምፓስ ሽንት ቤቶችስ ፅዳት ምን ይመስላል?

ስንቶቻችን ሽንት ቤት ከሄድን በኋላ ረስተን ሳንታጠብ ምግብ በላን ወይም የሰው እጅ ጨበጥን?

ጋንዲ እንዲህ ብሎ ነበር፦ የአከባቢ ንፅህና ከነፃነት በላይ ተፈላጊ ነው። ከህንዶች ጋር ከሚያቀራርቡን ነገሮች መካከል የንፅህና ጉደለታችን ተጠቃሽ ነው። እነሱም እንደኛ በየጉራንጉሩ የሚፀዳዱ ጉዶች ናቸው። በቦሊውድ ድራማ ተሸውዶ ህንድ የበለፀገችና ያማረች ሀገር አድርጎ የሚቆጥር ሰው ይኖራል። እውነታው ግን ህንድ በሽንት ቤት እጥረቷና በፅዳት ጉድለቷ ከነኮንጎ በታች ነች። ተርታዋ ከኛ ጎን ነው።

እየበሉ በአግብቡ መፀዳዳት አለመቻል አሳፋሪ ነው። ባንድ ጎን ረሃብ አንገት ሲያስደፋን በሌላው ጎን ደግሞ የፅዳት ማነስ ስማችንን ያሰድባል።

የሽንት ቤት ችግር ከሁሉም በላይ የሚያጠቃው ሴቶችን ነው። አብዛኛው ወንድ እንደነ ችሎማደር ግድግዳ እየተጠጋ መሽናትና መፀዳዳት ስለሚችል፥ የንፁህ ሽንት ቤት አለመኖር በሴቶች ላይ የሚያስከትለውን ችግር መገንዘብ አይችልም፥ የመገንዘብም ፍላጎት የለውም።

የአንድ ሀገር ማንነት ከሁሉም ነገር በላይ የሚለካው በፅዳት አያያዙ ነው። የረባ የሕዝብ ሽንትቤት ሳይኖረን ቱሪስቶችን ለመሳብ መፍጨርጨራችን ምን ይባላል? ከፈረሱ ጋሪውን ማስቀደም አይደለምን? ቱሪዝምና ሽንት ቤት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው። ስለ ሲንጋፖር ሳትሰሙ አትቀሩም መቼስ? የዚያች ሚጢጢ ሀገር ዋና የቱሪዝም ካረንሲዋ፥ ራሷን በፅዳት አንደኛ ብላ ማስተዋወቋ ነው። ውሸት ግን አይደለም። በየ መቶ ሜትሩ የመኖርያ ክፍል የሚመስሉ የውብ ሽንት ቤቶች ባለቤት ናት።

የኛ ሀገር የሽንት ቤት ሁኔታ ግን ተከድኖ ይብሰል። አብዛኛው የገጠሩ ህዝባችን ዛሬም ድረስ ሜዳ ላይ እንደሚፀዳዳ፥ ዛሬም ድረስ በቅጠል የሚጠርግ ሰው እንዳለ አንርሳ። — ወረቀትና ውሃ ከሌለ ይሞታል ወይ?

ኢንሻላህ! አንድ ቀን ሁሉም የሀገራችን ሰው አልፎለት በሶፍት ጠራጊ የሚሆንበት ቀን ይመጣ ይሆናል። እስከዛው እንግዲህ ኑሮ በዘዴው ይቀጥል…

ለማነኛውም መልካም የሽንት ቤት ቀን ይሁንል!

Screen shot 2015-11-19 at 7.10.59 AM

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s