ከፒዲዲ ወደ ፓፍዳዲ

ሰዉ ቀልድ በጣም ጨምሯል። የዳያስፖራው ሳይሆን ሀገር ውስጥ ያለው።

ሰሞኑን አንድ ዜና ከወደ አውሮፓ ተሰምቶ ነበር። ብሔር-ተኮር የሆነ የኢህአዴግን መንግስት አሽመደምዳለሁ የሚል አዲስ የፖለቲካ ጥምረት ተመስርቷል የሚል ዜና ነበር። መቼም እንደዚህ ዓይነት ዜና መስማት ጋዝ፣ ጋዝ እያለ ቢመጣም፥ የጥምረቱን ዜና ተንተርሶ ያሳቀኝ ነገር ስላገኘሁ ነው መጦመር ያማረኝ፤ የሸምሱ ሚስት “መቶ ብር አማረኝ” እንዳለችው።

ጥምረቱ ራሱን በፈረንጅኛ ምህፃረ ቃል PAFD ብሎ መሰየሙን ዜናው ያብራራል። የጥምረቱ ዓላማም ኢትዮጵያ ውስጥ “ነፃነትና ዲሞክራሲን” ማምጣትና የብሔር ብሔረሰቦችን “በራስ የመወሰን” መብት እውን ማድረግ መሆኑን ዜናው ገልጿል።

ጥምረቱን የመሰረቱት፣ በዕድሜ የገፉ ተሰብሳቢዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ ስብሰባው ላይ ካለመጠቀማቸው በተጨማሪ፥ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ሌሎች ወሳኝ ብሔሮችን ሳያሳትፉ ስለነፃነትና ዲሞክራሲ ዲስኩር ማሰማታቸው፥ ከወዲሁ የሚናገሩትንና የሚሰሩትን የማያውቁ አማተሮች መሆናቸውን አሳይተዋል። በሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ላይ ሊያመጡ የሚችሉት ተፅዕኖ ሊኖር እንደማይችልና ቢኖርም እርባናቢስ መሆኑን ተቺዎች ተናግረዋል።

በስብሰባው ላይ የነበሩት አብዛኞቹ ያፈጁ፣ያበጁ ሽማግሌ ወንዶች መሆናቸውን የተመለከተ አንድ ቀልደኛ የሚከተለውን ተረብ ለቆባቸው ነበር፦

“ጡረተኛ ሁላ እየተሰባሰበ ለራሱ ስራ ይፈጥራል። እቤት ተቀምጦ ከመተከዝ እንደዚህ እየተገናኙ ስለ ስኳራቸውና ደም ብዛታቸው ይጨዋወቱ።”

ሌላ ቀልደኛም ይህን ጨምሮ ነበር፦

“ከፒዲዲ ወደ ፓፍዳዲ የተሸጋገርንበት ሁኔታ ነው ያለው።”

እኔ ደግሞ፦ ብየያሳ (ብብቴን የኮረኮሩኝ ያህል ሳቅኩ)። በሌላ አገላለፅ LMAO።

ዘንድሮ መቼስ “ያለፕሮግራማችን የሚያስቁን” ሰዎች ተበራክተዋል። ዕድሜ ይስጠነ። “ኹሉ ንምርኣይ፥ ምቕናይ” እንዳለው፥ ያ አንጋፋ ድምጻዊ ኪሮስ አለማየሁ።

የዘመናችን ፖለቲከኛ በቃ እንዳሻው፣ ልክ እንደ አሜሪካውያን ሴሌብሪቲዎች በየሳምንቱ ይጣመራል፤ ይፋታል፤ ይጣመራል፤ ይፋታል። ከዳያስፖራው፣ ከነሶሮስ ድርጅቶችና ከአረቦች የሚገኝው የርዳታ ገንዘብ ምንጭ እስካልደረቀ ድረስ፥ ምን ችግር — ጥምረቱም፣ መፋታቱም ይቀጥላል።

እስኪ ደግሞ ልሂድና አንዳንድ ቱልቱላዎች በሚነፉት ጡሩንባ ልደበር። ኢት ኢዝ ቅዳሜ አፍተር ኦል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች። ትረስት ሚ። 🙂

image

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s