ሰው መሳይ አራዊት

ሰው መሳይ አራዊት
አለምን ገደሏት
ስቃይዋን አብዝተው
በካሜራቸው ፊት
ሴትነቷን ረግጠው
በሚሊዮኖች ፊት!

ቅስሟ ተሰብሮ
ህልሟ ታንኩሮ
ልቧ አምርሮ
ስብዕናዋ ተደፍሮ

ድረሱልኝ ብትል
ሰሚ ወገን አጥታ
የሕግ ያለህ ብትል
ደራሽ ወገን አጥታ
በነፍስ በላዎች
እህት ተንገላታ
ደም እያለቀሰች
ተስኗት መመለስ
እንደ ወጣች ቀረች
እኛን ልትቀሰቅስ!

በጨካኞች ገመድ
እየተጎተተች
በመኪና መንገድ
እየተረገጠች
በኤምባሲዋ ፊት
በቁም ስትዋረድ
ለምን አትመርጥ ሞት
ከጎኗ ሲጠፋ
አይዞሽ የሚል ዘመድ!

ሆኖም እንባዎቿ
በከንቱ አልፈሰሱም
ሆኖም ያ ጩኸቷ
ምድረበዳ አልቀረም
የተኛውን ሁሉ
ቀስቅሶ አንስቷል
ሌሎች ተበዳዮች
እንዳይረሱ አድርጓል!

አልቅሺ ኢትዮጵያ
አንቺ ምስኪን ሀገር
ልጆችሽን ዘርተሽ
በባእዳን ምድር
ባርነት ጣፈጠሽ
ያለምንም ማፈር
ነጻነትን ቀበርሽ
በድህነት ሰፈር!

ተባብሮ እንደመኖር
ተባብሮ እንደማደግ
የጥላቻ አረር
ስንታኮስ ትንታግ
አልምተን እንዳንከብር
ድንግሊቱን መሬት
ባህላችን ሆነ
አሳልፈን መስጠት
ሌላውን ማወፈር

ተሸካሚም መሆን
የባርነት ቀንበር
ሆነ ባህላችን
በልመና መኖር
ወይም ባሽከርነት
ለሰው መሳይ አራዊት!

***

PDF version: Sew Mesay Arawit by EMK

Advertisements

2 thoughts on “ሰው መሳይ አራዊት

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s