ሥብራት


በመንፈስ ሥብራት ቁስሌ አመርቅዞ
ምሬትን አርግዤ በጨለማው ጉዞ
ዓይኖች ሳያዩኝ ወደ ሲዖል መንደር
ዕዝኔ ቢያዳምጥም አፌ አይናገር

ሐዘንን የሚያርቅ ልቤ ፍቅር አጥቶ
ውስጤ ማቅ ለበሰ እንደ ጉም አጥልቶ
መንፈሴ አልሰክን እያለ ደንፍቶ
ደሜ ገነፈለ እንደ ቡና ፈልቶ

ልክ እንደ በረዶ እኔነት ቀዝቅዞ
ሰላሜ ተናጋ ተስፋዬ ደብዝዞ
ስሜቴም ለዘዘ አዕምሮዬ ፈዞ
ሞት ግን ፈነጠዘ መስሎት የምናዘዝ
እሱን ሳላወግዘው በቁሜ ምገነዝ

***

Advertisements

2 thoughts on “ሥብራት

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s