የወረት ፍቅር (momentary “love”) vs እውነተኛ ፍቅር (True Love)


የወረት “ፍቅር”
ውሎ አያድር
ለጊዜው ቢያሰክር
መለኪያው ግን
ጥቅም …
ምን አላት?
ምን አለው?
ምን ይመስላል?
ምን ትመስላለች?
መሪ ጥያቄው …

“ፍቅር” ያለ ሥራ
ውሃ በእንሥራ
“ፍቅር” ያለ ብር
አበባ ያለ ዘር

ሥራ የታጣ ለት
እንሥራ የተሰበረ ለት
“ፍቅርም” ውሃም ድፍት
ብር የጎደለ ለት
ዘር የጠፋ ለት
“ፍቅርም” አበባም አይኖሩት
ይሞታሉ ሳያብቡት

“ፍቅር” ያለ “ውበት”
አይረጋ አይሰነብት
አርቲፊሻል ውበት
ያሾቃል በወረት

“ለፍቅር” ነፃነት
ሀብት ማከማቸት
ጎጆ ሰሪው
ፆም አዳሪው
“ፍቅርን” ርሳው
“ፍቅር” ሄደ ወዳብታሙ
ባለጡንቻው ባለስሙ

***

እውነተኛ ፍቅር
በብር አይመነዘር
እንደ ወርቅ ይፈተናል
ሆኖም ግን ይጸናል
ከአልማዝ ያስንቃል
እንደ ብረት ይግላል
እንደ እሣት ይፋጃል
እውነተኛ ፍቅር ካለ
ገንዘቡ ይመጣል
ሀብት አዋሽ ይሆናል
እውነተኛ ፍቅር ካለ
አጥንት ይለመልማል
የገረጣ ፊት ይወዛል
ጡንቻ ይፈረጥማል
ደረትም ይሰፋል

ለመኖር በነፃነት
ፍቅርን መገብየት
ሚወዱትን መሥራት
አቅምን መገንባት
አብሮ መተጋገዝ
በትዕግስት መጓዝ
ችግርን አብሮ ማለፍ
ጨለማን ማሸነፍ

***

ወረት
እንደ ጨው ሙምት
ቢኖረው እንኳ ኮረት

***

ለመኖር በደስታ
በሣቅ በጫወታ
ለመኖር በምቾት
ጎጆ አብሮ ለመሥራት
አይሆንም በወረት
ገንዘብን በማምልክ
ለሀብት በመንበርከክ
ለውስጥ ውበት በመስገድ
ለውጩም በማበድ
አይሆንም አይሆንም
ቢሆንም አይጥምም
መምረሩ አይቀርም

***

የወረት “ፍቅር”
አቤት ሲያመናቅር

***

Advertisements

14 thoughts on “የወረት ፍቅር (momentary “love”) vs እውነተኛ ፍቅር (True Love)

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s