ዛሬን እንኑረው (Live in the now)


ያለፈው አልፎዋል
ነጌ ነገ ይመጣል
ሐሳብን እንርሳ
ይሙት ይህ ነቀርሳ
ዛሬን እንኑረው
ጥላሸት አንቀባው
ስቀን እንሸኘው

ቀን መምሸቱ ላይቀር
ሰው ዝም ብሎ ያብዳል
ሌት መንጋቱ ላይቀር
እንቅልፍ አጥቶ ያድራል
ተለፍቶ ተለፍቶ
ሁሉም ወደ ጉድጓድ
ያ ጊዜ ሳይመጣ
ተዉ እንዋደድ

ፍቅር ነው ሚሻለው
ጥላቻ በሽታ ነው
መቧጨቅ መናከስ
ላራዊት እንተወው
ከሐዘን እንራቅ
በማፍቅር በመሳቅ
እንደዛ ሲሆን ነው
ሕይወት የምታምረው
አለዚያ ግን ሞት ነው
በቁም መቀበር ነው

ጓዶቼ ቅረቡኝ
ከጎኔ አትራቁኝ
ፍቅሬም አትሽሺ
ነይ ከጄ ጉረሺ
ፍቅሬን ተረከቢ
ወደኔም ቅረቢ
ልብሽን ክፈቺው
የኔን እንድታይው

ሁሉም ዞሮ ዞሮ
መዝጊያው ያው ጭራሮ
ሁሉም በሮ በሮ
እንደ ቢራቢሮ
ሁሉም ኖሮ ኖሮ
ከሞት ጋር ቀጠሮ
መሆኑ ግልጽ ነው
ከንፈሬን ውሰጂው
ከንፈርሽን ልጉመጠው
እንደዚያ ሲሆን ነው
ህይወት የምትጥመው

ለሕይወት ዋጋ ንስጥ
ሰዎቼ አንቅበጥ
የፈሰሰ ውሃ
ስለማይታፈስ
ስሜት አያሸንፍ
ኅሊና እንዳይከስ
ሚሆነን ስናገኝ
በፍቅር እንጽና
እሱንም እሷንም
መጥበሱ ይቅርና

እኔ እወድሻለሁ
ከልቤ ካንጀቴ
እምልልሻለሁ
በምዬ በቴቴ
ካላመንሽ እንግዲ
ፈንጂ ገደል ግቢ …

***

Inspired by this song … 😀

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s