የጦጢት ስታይል

ቆይ፣ ቆይ አንተ፣ ጠብቅ!
እንደዚያ አይደለም፤
ምን ያስቸኩልሃል?
ቆየኝማ ልስተካከል!

እህ … ቆይ፣ ኧረ ቆይ፣
የሽቦ አጥሩ ላይ ልንጠልጠል፤
እሾሁ ግን እንዳይወጋኝ …
ኧረዲያልኝ!
“ሊያጌጡ ይመላለጡ”፥
አለች እመት ጉሬዛ፥
ነፍሷን ይማረውና።
እውነቷን ነው!
እሷስ ሃቁን ተናግራ አለፈች፤
መጥኔ ለኔ!
እስኪ ለማነኛውም፥
ፎቶዬን ማንሳትህ ካልቀረ
እንግዲህ በደንብ አንሳኝ …
አዎን … አሁን ትንሽ ተረጋጋህ፤
እንደዚያ ነው … በል አንሳኝ!

ቀጭ፣ ብልጭ አርገው፤
ለልጅ ልጆቼ
ሞቼ እንዳልሞትባቸው።
ጸዳ ያለ ምስል፥
ያ ነው የኔ ስታይል!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s