ሁለት ቦታ ኑሮ

የማር ወተት ባሕር — በሕልም ካየሁ ወዲህ
መንፈሴ ሄደዛ — ሥጋዬ ግን እዚህ
በሐሳቤ ርቄ — ሽምጥ ጋልባለሁ
በድኔ ተሸክሞኝ — እፈረጥጣለሁ

pic via lightiscolor.com

ለማላውቀው ዓለም — አጥቻለሁ እንቅልፍ
በርሬ ሄዳለሁ — በቅዠታለም ክንፍ
በሕልሜ ሮጣለሁ — የትም ለማልደርሰው
ምኞት ፍላጎቴ — እዛ መገኘት ነው
እዛ ያለው ሞኝ ግን — ወደዚህ ያስባል
ጥፍጥና ሰልችቶት — “ወዳገርቤት” ይላል
የኔግር ኬንያን — ለማቋረጥ ቋምጧል
የሱ እግር ደግሞ — ወደዚ ያማትራል
አቧራ፣ ቁንጫ — ሙጀሊትን ናፍቋል

ወየው ጉድ ዘንድሮ
ሁለት ቦታ ኑሮ
ውስጤ አሮ፣ አሮ
አሮ፣ ተኮማትሮ
ሆኛለሁ አሻሮ

ለአሥራ ዓመታት — እዚህ ሀገር ኖሬ
የማር ወተት ባሕር — አላየሁ እስከዛሬ
ለፋለሁ፣ ተጋለሁ — ኖራለሁ አምርሬ
ሁሌ ትዝ እያለኝ — የትውልድ መንደሬ

ከዚህ አልተቀየጥኩ — ወይ አልሄድኩኝ እዛ
መሐል ላይ ቆሜያለሁ — እንዳገሬ ዋንዛ
የወንዜ ልጅ ደግሞ — የኔ ሲዖል ናፍቆት
የማር ወተት ባሕር — ያልማል ሳይታክት
በድን ሆኖ ቀርቷል — ነፍሱን እዚህ ልኳት
መጥቶ ስላላየው — የ’ልምን ቅዠትነት
እኔን ግን የራበኝ — የእናቴ ውበት፣ የእናቴ ፍካት
እኔን የናፈቀኝ — በሀገሬ ማለም፣ በሀገሬ መሥራት
(ያሰኘኝ ‘ለት ብቻ — መግባትና መውጣት!)
ያ ነው የኔ ህመም — ፊቴን ያገረጣኝ
ከጥፍጥና አጣልቶ — መራራ ያረገኝ
አሁን ልመለስ ብል — it’s f-ing late!
ባዶ እጅ ጉዞ — በምን ዓይኔ ላያት?
እንደወጣሁ ቀረሁ — አልሜ ማር፣ ወተት

ወየው ጉድ ዘንድሮ
ሁለት ቦታ ኑሮ
ውስጤ አሮ፣ አሮ
አሮ፣ ተኮማትሮ
ሆኛለሁ አሻሮ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s