የሰውነት ልኩ በሥጋ ሲመተር

ከሲታ ኮሰሴ አጥንቱ ‘ሚዋጋው
እግሩ የሰለለ ፊቱ የገረጣው
ዓይኑ የጎረጎደ ምግብ ‘ማይጠጋው
አየ ስትሸማቅ ሲቀመጡ አብረው
ሰው ባለፈ ቁጥር እንደቃ ስትቆጥረው።

ወፈረ ቀጠነ እሱ ደንታ የለው
ጭንቁ ለነብሱ ‘ንጂ አይደለም ለሥጋው
አካሏን ‘ማታከብር የሱን ግን ስትንቅ
ጥሏት ብድግ አለ ካጠገቧም ፈቀቅ
የውስጡን ‘ምታይ …
ራሷንም ‘ምታከብር ልቡ እስኪተዋወቅ።

ሲቀጥኑ መከራ ሲወፍሩም ችግር
የሰውነት ልኩ በሥጋ ሲመተር
አንዳንዱ ይገደዳል በራሱ እንዲያፍር
ሁሌ ይጨቀጨቃል ክብደቱ እንዲቀንስ
ወይም እንዲጨምር …
የዘመኑ ነገር።

የሱ ደ—ስታ ግን ተቃራኒ መሆን
ውፍረቱ ሲፈለግ እንደ ሰርዶ መቅጠን
ወይም እንደ ዘንዶ ነጋ ጠባ መዋጥ
መቅጠን ሲኖርበት ወፍሮ መቀመጥ
መወፈር መቅጠኑ ጤናውን ካልረታ
እነሱ ይጨነቁ እሱ የለው ደንታ!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s