አይሻልም ወይ ጊዜን መዋጀት?

ያመኑበትን እያስከበሩ
ያላመኑበትን እያስመነጠሩ
የጥንቶቹ ጥንት ሲቀሩ
የዛሬዎቹ በተራቸው
አዲስ እምነትን ፈጠሩ
እስኪያልፉ ሊተገብሩ
“በድሮ በሬ አይታረስም”
እንዳለው ባላገሩ

የጥንቱን እየናፈቁ
ከመንደድ ከመቃጠል
የዛሬውን እንደ ድሮው
ለማድረግ ከመታገል
ከጊዜ ጋር መራመድ
የአሁኑን መላመድ
ወይም ማርበድበድ
አይሻልም ወይ ጊዜን መዋጀት
ወደፊት መጓዝ መሄድ
እንደ ጥንት ዛር ከማጓራት?

ኤል ያስ

Advertisements

2 thoughts on “አይሻልም ወይ ጊዜን መዋጀት?

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s